ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 11:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከእሴይ ግንድ ቍጥቋጥ ይወጣል፤ከሥሮቹም አንዱ ቅርንጫፍ ፍሬ ያፈራል።

2. የእግዚአብሔር መንፈስ፣የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣የምክርና የኀይል መንፈስ፣የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።

3. እግዚአብሔርን በመፍራት ደስ ይለዋል፤ዐይኑ እንዳየ አይፈርድም፤ጆሮውም እንደ ሰማ አይበይንም።

4. ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።

5. ጽድቅ የወገቡ መታጠቂያ፣ታማኝነትም የጐኑ መቀነት ይሆናል።

6. ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይኖራል፤ነብርም ከፍየል ግልገል ጋር ይተኛል፤ጥጃ፣ የአንበሳ ደቦልና የሰባ ከብት በአንድነት ይሰማራሉ፤ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል።

7. ላምና ድብ በአንድነት ይሰማራሉ፤ልጆቻቸውም አብረው ይተኛሉ፤አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል።

8. ጡት የሚጠባ ሕፃን በአደገኛ እባብ ጒድጓድ ላይ ይጫወታል፤ጡት የጣለም ሕፃን እጁን በእፉኝት ጒድጓድ ይከትታል።

9. በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ ጒዳት ወይም ጥፋት አያደርሱም፤ውሃ ባሕርን እንደሚሸፍን፣ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን በማወቅትሞላለችና።

10. በዚያን ቀን፣ የእሴይ ሥር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ መንግሥታት ወደ እርሱ ይመጣሉ፤ ማረፊያውም የከበረ ይሆናል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 11