ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አስቴር 6:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ሐማ በገባ ጊዜ ንጉሡ፣ “ንጉሥ ሊያከብረው ለወደደው ሰው ምን ሊደረግለት ይገባል?” ሲል ጠየቀው።በዚህ ጊዜ ሐማ፣ “ንጉሡ ከእኔ ይልቅ የሚያከብረው ማን አለ?” ሲል በልቡ ዐሰበ።

7. ስለዚህ ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ንጉሡ ሊያከብረው ለወደደው ሰው፣

8. ንጉሡ የሚጐናጸፈው ልብሰ መንግሥት፣ ንጉሡም የሚቀመጥበትና የንጉሡን ዘውድ በራሱ ላይ ያደረገ ፈረስ ይምጣለት።

9. ከዚያም ልብሱና ፈረሱ እጅግ ከከበሩት ከንጉሡ ልዑላን መሳፍንት በአንዱ እጅ ይሰጥለት። ንጉሡ ሊያከብረው የወደደውን ሰው ያልብሱት፤ በፈረሱም ላይ አስቀመጠውም በከተማዪቱ ዋና ዋና መንገዶች ላይ እየመሩ፣ ‘ንጉሡ ሊያከብረው ለሚወደው ሰው ይህ ተደርጎለታል’ ይበሉ።”

10. ንጉሡም ሐማን፣ “በል ፈጥነህ ሂድ፤ ልብሱንና ፈረሱን ውሰድ፤ በንጉሡ በር ላይ ለሚቀመጠው ለአይሁዳዊው ለመርዶክዮስም ልክ እንዳልኸው አድርግለት፤ ከተናገርኸውም አንዳች ነገር እንዳይጐድል” ሲል አዘዘው።

11. ስለዚህ ሐማ ልብሱንና ፈረሱን ወስዶ መርዶክዮስን አለበሰው፤ በዋና ዋና መንገዶች ላይ እየመራም፣ “ንጉሥ ሊያከብረው ለሚወደው ሰው ይህ ተደርጎለታል” እያለ በፊቱ ያውጅ ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አስቴር 6