ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ነህምያ 12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ካህናትና ሌዋውያን

1. ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋር የተመለሱት ካህናትና ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤ሠራያ፣ ኤርምያስ፣ ዕዝራ፣

2. አማርያ፣ መሉክ፣ ሐጡስ፣

3. ሴኬንያ፣ ሬሁም፣ ሜሪሞት፣

4. አዶ፣ ጌንቶን፣ አብያ፣

5. ሚያሚን፣ መዓድያ፣ ቢልጋ፣

6. ሸማያ፣ ዮያሪብ፣ ዮዳኤ፣

7. ሰሉ፣ ዓሞቅ፣ ኬልቅያስና ዮዳኤ።እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው አለቆች ነበሩ።

8. ሌዋውያኑ ደግሞ ኢያሱ፣ ቢንዊ፣ ቀድምኤል፣ ሰራብያ፣ ይሁዳ እንዲሁም ከወንድሞቹ ጋር የምስጋና መዝሙር ኀላፊ የሆነው መታንያ ነበሩ።

9. ወንድሞቻቸው የሆኑት በቅቡቅያና ዑኒም በአገልግሎት ጊዜ ከእነርሱ ትይዩ ይቆሙ ነበር።

10. ኢያሱ ዮአቂምን ወለደ፤ ዮአቂም ኤልያሴብን ወለደ፤ ኤልያሴብ ዮአዳን ወለደ፤

11. ዮአዳ ዮናታንን ወለደ፤ ዮናታንም ያዱአን ወለደ።

12. በዮአቂም ዘመን የካህናቱ ቤተ ሰብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ከሠራያ ቤተ ሰብ፣ ምራያ፤ከኤርምያስ፣ ሐናንያ፤

13. ከዕዝራ፣ ሜሱላም፤ከአማርያ፣ ይሆሐናን፤

14. ከሙሊኪ፣ ዮናታን፤ከሰብንያ፣ ዮሴፍ፤

15. ከካሪም፣ ዓድና፤ከመራዮት፣ ሔልቃይ፤

16. ከአዶ፣ ዘካርያስ፤ከጌንቶን፣ ሜሱላም፤

17. ከአብያ፣ ዝክሪ፤ከሚያሚንና ከሞዓድያ፣ ፈልጣይ፤

18. ከቢልጋ፣ ሳሙስ፤ከሸማያ፣ ዮናታን፤

19. ከዮያሪብ፣ መትናይ፤ከዮዳኤ፣ ኦዚ፤

20. ከሳላይ፣ ቃላይ፤ከዓሞቅ፣ ዔቤር፤

21. ከኬልቅያስ፣ ሐሸብያ፤ከዮዳኤ፣ ናትናኤል።

22. በኤሊያሴብ፣ በዮአዳ፣ በዮሐናንና በያዱአ ዘመን የሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆችና ካህናቱ፣ በፋርሳዊው በዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ተመዝግበው ነበር።

23. ከሌዋውያን ዘሮች መካከል እስከ ኤሊያሴብ ልጅ እስከ ዮሐናን ድረስ ያሉት የየቤተ ሰቡ ኀላፊዎች በታሪክ መጽሐፍ ተመዝግበው ነበር።

24. የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሸብያ፣ ሰራብያ፣ የቀድምኤል ልጅ ኢያሱ ነበሩ፤ እነርሱም ከወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት እየተቀባበሉ ውዳሴና ምስጋና ያቀርቡ ነበር።

25. በቅጥሩ በሮች አጠገብ ያሉትን ዕቃ ቤቶች የሚጠብቁት ዘቦች ደግሞ መታንያ፣ በቅቡቅያ፣ አብድዩ፣ ሜሱላም፣ ጤልሞንና ዓቁብ ነበሩ።

26. እነዚህም በኢዮሴዴቅ ልጅ፣ በኢያሱ ልጅ በዮአቂም፣ በአገረገዢ በነህምያ፣ በካህኑና በጸሓፊው በዕዝራ ዘመን አገለገሉ።

የኢየሩሳሌም ቅጥር ምረቃ በዓል

27. የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲመረቅ ሌዋውያኑ በምስጋና መዝሙር፣ በጸናጽል፣ በበገናና በመሰንቆ ድምፅ የምረቃውን በዓል በደስታ እንዲያከብሩ ከሚኖሩበት ተፈልገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

28. መዘምራኑንም እንደዚሁ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለው ከነጦፋውያን መንደሮች በአንድነት ሰበሰቧቸው።

29. በኢየሩሳሌም ዙሪያ የራሳቸውን መንደሮች ሠርተው ስለ ነበር፣ መዘምራኑን ያመጧቸው ከቤት ጌልገላ፣ ከጌባና ከዓዝምት አካባቢ ነው።

30. ካህናቱና ሌዋውያኑ በሥርዐቱ መሠረት ራሳቸውን ካነጹ በኋላ፣ ሕዝቡን፣ ቅጥሩና በሮቹን አነጹ።

31. እኔም የይሁዳን መሪዎች በቅጥሩ ግንብ አናት ላይ እንዲወጡ አደረግሁ፤ ደግሞም ምስጋና እንዲያቀርቡ ሁለት ታላላቅ የመዘምራን ቡድን መደብሁ። አንዱ በቅጥሩ ግንብ አናት በስተ ቀኝ በኩል “ቈሻሻ መጣያ በር” ወደሚባለው ሄደ።

32. እነዚህንም ሆሻያና ከይሁዳ አለቆች እኩሌቶቹ ተከተሏቸው፤

33. የተከተሏቸውም ከዓዛርያስ፣ ከዕዝራ፣ ከሜሱላም፣

34. ከይሁዳ፣ ከብንያም፣ ከሸማያ፣ ከኤርምያስና፣

35. እንዲሁም መለከት ከያዙ ጥቂት ካህናትና ከአሳፍ ልጅ፣ ከዘኩር ልጅ፣ ከሚካያ ልጅ ከመታንያ ልጅ፣ ከሸማያ ልጅ፣ ከዮናታን ልጅ፣ ከዘካርያስ ጋር ነበር።

36. ወንድሞቹ ሸማያ፣ ኤዝርኤል፣ ሚላላይ፣ ጊላላይ፣ መዓይ፣ ናትናኤል፣ ይሁዳና አናኒም የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ባዘዘው መሠረት የዜማ መሣሪያዎቹን ይዘው ሄዱ፤ ሰልፉን የሚመራውም ጸሓፊው ዕዝራ ነበረ።

37. “ከምንጭ በር” ተነሥተው በቀጥታ ወደ “ዳዊት ከተማ” ደረጃዎች ወጡ፤ ከዚያም በቅጥሩ መውጫ በኩል አድርገው ከዳዊት ቤት በላይ በስተ ምሥራቅ ወደሚገኘው ወደ “ውሃ በር” ሄዱ።

38. ሁለተኛው የመዘምራን ቡድን በስተ ግራ በኩል ሄደ፤ እኔም ከከፊሉ ሕዝብ ጋር ሆኜ በቅጥሩ ግንብ ላይ፣ የእቶኑን ግንብ በማለፍ እስከ ሰፊው ቅጥር ተከተልኋቸው፤

39. ከዚያም ከኤፍሬም በር በላይ፣ በአሮጌ በር፣ በዓሣ በር፣ በሐናንኤል ግንብ፣ በመቶዎቹ ግንብ አልፌ እስከ “በጎች በር” ድረስ ተከተልኋቸው። እነርሱም “በዘበኞች በር” አጠገብ ሲደርሱ ቆሙ።

40. ቀጥሎም ምስጋና ያቀረቡት ሁለቱ የመዘምራን ቡድኖች፣ በእግዚአብሔር ቤት ቦታቸውን ያዙ፤ እኔም ከግማሾቹ ሹማምት ጋር ቦታዬን ያዝሁ፤

41. እንደዚሁም ካህናቱ ኤልያቄም፣ መዕሤያ፣ ሚንያሚን፣ ሚካያ፣ ኤልዮዔናይ፣ ዘካርያስና ሐናንያ መለከታቸውን ይዘው፣

42. መዕሤያ፣ ሸማያ፣ አልዓዛር፣ ኦዚ፣ ይሆሐናን፣ መልክያ፣ ኤላምና ኤጽር ቦታቸውን ያዙ፤ መዘምራኑ በይዝረሕያ መሪነት ዘመሩ።

43. እግዚአብሔር ታላቅ ደስታ ስለሰጣቸው፣ በዚያች ዕለት ደስ ብሏቸው ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሴቶችና ልጆችም እንደዚሁ ደስ አላቸው፤ ከዚህም የተነሣ በኢየሩሳሌም የነበረው የደስታ ድምፅ እስከ ሩቅ ድረስ ይሰማ ነበር።

44. በዚያን ቀን ስጦታው፣ በኵራቱና ዐሥራቱ የሚቀመጥበት ዕቃ ቤት የሚጠብቁ ሰዎች ተሾሙ። እነርሱም በየከተሞች ዙሪያ ከሚገኙት የእርሻ ቦታዎች ሕጉ በሚያዘው መሠረት የካህናቱንና የሌዋውያኑን ድርሻ ወደ ዕቃ ቤቱ ማምጣት ነበረባቸው፤ ይሁዳ በሚያገለግሉ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ተሰኝተው ነበርና።

45. እንደ መዘምራኑና በር ጠባቂዎቹ ሁሉ፣ እነዚህም የአምላካቸውን አገልግሎትና የመንጻቱን ሥርዐት በዳዊትና በልጁ በሰሎሞን ትእዛዝ መሠረት ፈጸሙ።

46. ቀድሞ በዳዊትና በአሳፍ ዘመን ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን የውዳሴ መዝሙሮችና ምስጋና የሚመሩ የመዘምራን አለቆች ነበሩ።

47. በዘሩባቤልና በነህምያም ዘመን እስራኤል ሁሉ ለመዘምራኑና ለበር ጠባቂዎቹ የየዕለቱን ድርሻ ይሰጡ ነበር፤ የሌሎቹን ሌዋውያን ድርሻም ለብቻ ያስቀምጡ ነበር፤ ሌዋውያኑም ለአሮን ዘሮች ድርሻቸውን ያስቀምጡላቸው ነበር።