ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሶፎንያስ 2:8-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. “የሞዓብን ስድብ፣የአሞናውያንንም ፌዝ ሰምቻለሁ፤ሕዝቤን ሰድበዋል፤በምድራቸውም ላይ ዝተዋል።

9. ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በሕያውነቴ እምላለሁሞዓብ እንደ ሰዶም፣አሞናውያን እንደ ገሞራ፣ዐረም እንደ ዋጠው ቦታና እንደ ጨውጒድጓድ ለዘላለም ጠፍ ይሆናሉ።ከሕዝቤ የቀሩት ይዘርፏቸዋል፤ከወገኔ የተረፉትም ምድራቸውንይወርሳሉ።”

10. ከትዕቢታቸው የተነሣ የሚደርስባቸው ይህ ነው፤የሁሉን ገዥ የእግዚአብሔርን ሕዝብሰድበው ዘብተውበታልና፣

11. እግዚአብሔር የምድሪቱን አማልክትሁሉ በሚደመስስበት ጊዜ፣በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤በየባሕሩ ጠረፍ የሚኖሩ ሕዝቦች፣እያንዳንዳቸው በያሉበት ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።

12. “ኢትዮጵያውያን ሆይ፤ እናንተም፣በሰይፌ ትገደላላችሁ።”

13. እጁን በሰሜን ላይ ይዘረጋል፤አሦርንም ያጠፋል፤ነነዌን ፍጹም ባድማ፣እንደ ምድረ በዳም ደረቅ ያደርጋታል።

14. የበግና የከብት መንጋዎች፣የፍጥረት ዐይነት ሁሉ በውስጧ ይመሰጋሉ፤ጒጒትና ጃርት፣በግንቦቿ ላይ ያድራሉ።ጩኸታቸው በየመስኮቱ ያስተጋባል፤ፍርስራሽ በየደጃፉ ይከመራል፤ከዝግባ የተሠሩ ተሸካሚዎችም ይገለጣሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሶፎንያስ 2