የበግና የከብት መንጋዎች፣የፍጥረት ዐይነት ሁሉ በውስጧ ይመሰጋሉ፤ጒጒትና ጃርት፣በግንቦቿ ላይ ያድራሉ።ጩኸታቸው በየመስኮቱ ያስተጋባል፤ፍርስራሽ በየደጃፉ ይከመራል፤ከዝግባ የተሠሩ ተሸካሚዎችም ይገለጣሉ።