ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሶፎንያስ 2 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እናንት ዕረፍት የሌላችሁ ሕዝብ ሆይ፤በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ተከማቹም፤

2. የተወሰነው ጊዜ ሳይደርስ፣ቀኑ እንደ ገለባ ሳይጠራርጋችሁ፣ የእግዚአብሔር ጽኑ ቊጣ በእናንተ ላይ ሳይመጣ፣ የእግዚአብሔር የመዓት ቀንሳይደርስባችሁ ተሰብሰቡ።

3. እናንት የምድር ትሑታን ሁሉ፣ትእዛዙን የምትፈጽሙ፣ እግዚአብሔርን እሹ፤ጽድቅንና ትሕትናን ፈልጉ፤ በእግዚአብሔር የቊጣ ቀን፣ትሰወሩ ይሆናል።

በፍልስጥኤም ላይ የተነገረ ጥፋት

4. ጋዛ ባድማ ትሆናለች፤አስቀሎናም ፈራርሳ ትቀራለች፤አዛጦን በቀትር ባዶ ትሆናለች፤አቃሮንም ትነቀላለች።

5. እናንት በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ፣የከሊታውያን ሰዎች ሆይ፤ ወዮላችሁየፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፤በአንቺ ላይ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤“ፍጹም አጠፋሻለሁ፤ከነዋሪዎችሽም የሚተርፍ የለም።”

6. የቀርጤስ ሰዎች የሚኖሩበት በባሕሩዳር ያለው ምድር፣የእረኞች መኖሪያና የበጎች በረት ይሆናል፤

7. ይህም ለይሁዳ ቤት ትሩፍ ይሰጣል፤እነርሱም በዚያ መሰማሪያ ያገኛሉ።በአስቀሎና ቤቶች ውስጥም፣በምሽት ይተኛሉ፤አምላካቸው እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፤ምርኮአቸውንም ይመልስላቸዋል።

በሞዓብና በአሞን ላይ የተነገረ ጥፋት

8. “የሞዓብን ስድብ፣የአሞናውያንንም ፌዝ ሰምቻለሁ፤ሕዝቤን ሰድበዋል፤በምድራቸውም ላይ ዝተዋል።

9. ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በሕያውነቴ እምላለሁሞዓብ እንደ ሰዶም፣አሞናውያን እንደ ገሞራ፣ዐረም እንደ ዋጠው ቦታና እንደ ጨውጒድጓድ ለዘላለም ጠፍ ይሆናሉ።ከሕዝቤ የቀሩት ይዘርፏቸዋል፤ከወገኔ የተረፉትም ምድራቸውንይወርሳሉ።”

10. ከትዕቢታቸው የተነሣ የሚደርስባቸው ይህ ነው፤የሁሉን ገዥ የእግዚአብሔርን ሕዝብሰድበው ዘብተውበታልና፣

11. እግዚአብሔር የምድሪቱን አማልክትሁሉ በሚደመስስበት ጊዜ፣በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤በየባሕሩ ጠረፍ የሚኖሩ ሕዝቦች፣እያንዳንዳቸው በያሉበት ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።

በኢትዮጵያ ላይ የተነገረ ጥፋት

12. “ኢትዮጵያውያን ሆይ፤ እናንተም፣በሰይፌ ትገደላላችሁ።”

በአሦር ላይ የተነገረ ጥፋት

13. እጁን በሰሜን ላይ ይዘረጋል፤አሦርንም ያጠፋል፤ነነዌን ፍጹም ባድማ፣እንደ ምድረ በዳም ደረቅ ያደርጋታል።

14. የበግና የከብት መንጋዎች፣የፍጥረት ዐይነት ሁሉ በውስጧ ይመሰጋሉ፤ጒጒትና ጃርት፣በግንቦቿ ላይ ያድራሉ።ጩኸታቸው በየመስኮቱ ያስተጋባል፤ፍርስራሽ በየደጃፉ ይከመራል፤ከዝግባ የተሠሩ ተሸካሚዎችም ይገለጣሉ።

15. ተዘልላ የኖረች፣ደስተኛዪቱ ከተማ ይህች ናት፤እርሷም በልቧ፣“እኔ ብቻ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ማንም የለም” ያለች፣ታዲያ እንዴት የዱር አራዊት የሚመሰጉባት፣ባድማ ሆና ቀረች?በአጠገቧ የሚያልፉ ሁሉ፣ያፌዙባታል፤ እጃቸውንም በንቀት ያወዛውዙባታል።