ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 7:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ለእኔ ወዮልኝ!የወይን ዕርሻ በሚቃረምበት ጊዜየበጋ ፍራፍሬ እንደሚለቅም ሰው ሆኛለሁ፤የሚበላ የወይን ዘለላ የለም፤የምንጓጓለት፣ ቶሎ የሚደርሰው በለስም አልተገኘም።

2. ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረበት ሰው ከምድር ጠፍቶአል፤አንድም እንኳ ቅን ሰው የለም፣ሰው ሁሉ ደም ለማፍሰስ ያደባል፤እያንዳንዱም ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል።

3. እጆቹ ክፉ ለማድረግ ሠልጥነዋል፤ገዡ እጅ መንሻ ይፈልጋል፤ፈራጁ ጒቦ ይቀበላል፤ኀይለኞች ያሻቸውን ያስፈጽማሉ፤ሁሉም አንድ ላይ ያሤራሉ።

4. ከእነርሱ ይሻላል የተባለው እንደ አሜከላ፣እጅግ ቀና የተባለውም እንደ ኵርንችት ነው፤የጠባቂዎቻችሁ ቀን ደርሶአል፤የእግዚአብሔር የፍርድ ቀን መጥቶአል፤የሚሸበሩበትም ጊዜ አሁን ደርሶአል።

5. ባልንጀራህን አትመን፤በጓደኛህም አትታመን፤በዕቅፍህ ለምትተኛዋ እንኳ፣ስለምትነግራት ቃል ተጠንቀቅ።

6. ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃል፤ሴት ልጅ በእናቷ ላይ፤ምራት በአማቷ ላይ ትነሣለች፤የሰው ጠላቶች የገዛ ቤተ ሰዎቹ ናቸውና።

7. እኔ ግን እግዚአብሔርን ተስፋ አደርጋለሁ፤አዳኜ የሆነውን አምላክ እጠብቃለሁ፤አምላኬ ይሰማኛል።

8. ጠላቴ ሆይ፤ በእኔ ላይ በደረሰው ደስ አይበልሽ!ብወድቅም እንኳ እነሣለሁ፤በጨለማ ብቀመጥ እንኳ፣ እግዚአብሔር ብርሃኔ ይሆናል።

9. እርሱን ስለ በደልሁ፣እስኪቆምልኝእስኪፈርድልኝም ድረስ፣ የእግዚአብሔርን ቊጣ እቀበላለሁ፤እርሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤እኔም ጽድቁን አያለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 7