ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 7:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ለእኔ ወዮልኝ!የወይን ዕርሻ በሚቃረምበት ጊዜየበጋ ፍራፍሬ እንደሚለቅም ሰው ሆኛለሁ፤የሚበላ የወይን ዘለላ የለም፤የምንጓጓለት፣ ቶሎ የሚደርሰው በለስም አልተገኘም።

2. ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረበት ሰው ከምድር ጠፍቶአል፤አንድም እንኳ ቅን ሰው የለም፣ሰው ሁሉ ደም ለማፍሰስ ያደባል፤እያንዳንዱም ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል።

3. እጆቹ ክፉ ለማድረግ ሠልጥነዋል፤ገዡ እጅ መንሻ ይፈልጋል፤ፈራጁ ጒቦ ይቀበላል፤ኀይለኞች ያሻቸውን ያስፈጽማሉ፤ሁሉም አንድ ላይ ያሤራሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 7