ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 55:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ልመናዬን ቸል አትበል፤

2. ወደ እኔ ተመልከት፤ መልስልኝም።በውስጤ ታውኬአለሁ፤ ተናውጬአለሁም፤

3. በጠላት ድምፅ ተሸበርሁ፤በክፉዎች ድንፋታ ደነገጥሁ፤መከራ አምጥተውብኛልና፤በቍጣም ተነሣሥተው ጠላት ሆነውብኛል።

4. ልቤ በውስጤ ተጨነቀብኝ፤የሞት ድንጋጤም በላዬ መጣ።

5. ፍርሀትና እንቅጥቃጤ መጣብኝ፤ሽብርም ዋጠኝ።

6. እኔም እንዲህ አልሁ፤ “ምነው የርግብ ክንፍ በኖረኝ!በርሬ በሄድሁና ባረፍሁ ነበር፤

7. እነሆ፤ ኰብልዬ በራቅሁ፣በምድረ በዳም በሰነበትሁ ነበር፤ ሴላ

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 55