ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 31:6-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. የሰማይ ወፎች ሁሉ፣በቅርንጫፎቹ ላይ ጐጆአቸውን ሠሩ፤የምድር አራዊት ሁሉ፣ከቅርንጫፎቹ ሥር ግልገሎቻቸውን ወለዱ።ታላላቅ መንግሥታትም ሁሉ፣ከጥላው ሥር ኖሩ።

7. ከተንሰራፉት ቅርንጫፎቹ ጋር፣ውበቱ ግሩም ነበር፤ብዙ ውሃ ወዳለበት፣ሥሮቹ ጠልቀው ነበርና።

8. በእግዚአብሔር ገነት ያሉ ዝግባዎች፣ሊወዳደሩት አልቻሉም፤የጥድ ዛፎች፣የእርሱን ቅርንጫፎች አይተካከሉትም፤የአስታ ዛፎችም፣ከእርሱ ቅርንጫፎች ጋር አይወዳደሩም፤በእግዚአብሔር ገነት ያለ ማናቸውም ዛፍ፣በውበት አይደርስበትም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 31