ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40
  41. 41
  42. 42
  43. 43
  44. 44
  45. 45
  46. 46
  47. 47
  48. 48

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የሊባኖስ ዝግባ

1. በዐሥራ አንደኛው ዓመት፣ በሦስተኛው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

2. “የሰው ልጅ ሆይ፤ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖንና ስፍር ቍጥር ለሌለው ሕዝቡ እንዲህ በል፤“ ‘በክብር ከአንተ ጋር ማን ሊወዳደር ይችላል፤

3. ለጫካው ጥላ የሆኑ የሚያማምሩ ቅርንጫፎች የነበሩትን፣እጅግ መለሎ ሆኖ፣ጫፉ ሰማይ የደረሰውን፣የሊባኖስን ዝግባ አሦርን ተመልከት።

4. ውሆች አበቀሉት፤ጥልቅ ምንጮች አሳደጉት፤ጅረቶቻቸው ፈሰሱ፤የሥሮቹንም ዙሪያ ሁሉ አረሰረሱ፤በመስኩ ላይ ወዳሉት ዛፎች ሁሉ፣መስኖዎቻቸውን ለቀቁት።

5. ስለዚህ በደን ካሉት ዛፎች ሁሉ፣እጅግ ከፍ አለ፤ቅርንጫፎቹ በዙ፤ቀንበጦቹ ረዘሙ፤ከውሃውም ብዛት የተነሣ ተስፋፉ።

6. የሰማይ ወፎች ሁሉ፣በቅርንጫፎቹ ላይ ጐጆአቸውን ሠሩ፤የምድር አራዊት ሁሉ፣ከቅርንጫፎቹ ሥር ግልገሎቻቸውን ወለዱ።ታላላቅ መንግሥታትም ሁሉ፣ከጥላው ሥር ኖሩ።

7. ከተንሰራፉት ቅርንጫፎቹ ጋር፣ውበቱ ግሩም ነበር፤ብዙ ውሃ ወዳለበት፣ሥሮቹ ጠልቀው ነበርና።

8. በእግዚአብሔር ገነት ያሉ ዝግባዎች፣ሊወዳደሩት አልቻሉም፤የጥድ ዛፎች፣የእርሱን ቅርንጫፎች አይተካከሉትም፤የአስታ ዛፎችም፣ከእርሱ ቅርንጫፎች ጋር አይወዳደሩም፤በእግዚአብሔር ገነት ያለ ማናቸውም ዛፍ፣በውበት አይደርስበትም።

9. በብዙ ቅርንጫፎች፣ውብ አድርጌ ሠራሁት፤በእግዚአብሔርም የአትክልት ቦታ፣በገነት ያሉትን ዛፎች የሚያስቀና አደረግሁት።

10. “ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጥቅጥቅ ባለው ቅጠል ላይ ጫፉን ከፍ በማድረግ ራሱን በማንጠራራቱ፣ በርዝማኔውም በመኵራራቱ፣

11. እንደ ክፋቱ መጠን የሥራውን ይከፍለው ዘንድ፣ ለአሕዛብ ገዥ አሳልፌ ሰጠሁት። አውጥቼ ጥየዋለሁ፤

12. ከአሕዛብ ወገን እጅግ ጨካኝ የሆኑትም ባዕዳን ሰዎች ቈራርጠው ጣሉት። ቀንበጦቹ በተራራዎቹና በሸለቆዎቹ ሁሉ ላይ ወድቀዋል፤ ቅርንጫፎቹም በውሃ መውረጃዎቹ ሁሉ ላይ ተሰባብረው ወድቀዋል፤ የምድሪቱ ሰዎች ሁሉ ከጥላው ሥር በመውጣት ትተውት ሄደዋል።

13. የሰማይ ወፎች ሁሉ በወደቀው ዛፍ ላይ ሰፈሩ፤ የምድር አራዊት ሁሉ በወደቀው ዛፍ ቅርንጫፎች ላይ ሰፈሩ።

14. ስለዚህ በውሃ አጠገብ ያለ ማንኛውም ዛፍ፣ ጫፎቹን ችምችም ካለው ቅጠል በላይ ከፍ በማድረግ፣ ከእንግዲህ ራሱን በትዕቢት አያንጠራራም። ከእንግዲህ ውሃ በሚገባ ያገኘ ማንኛውም ዛፍ ወደዚህ ዐይነቱ ከፍታ አይደርስም። ሁሉም ከምድር በታች ወደ ጒድጓድ ከሚወርድ ሟች ጋር አብሮ እንዲሞት ተወስኖበታልና።”

15. “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ወደ መቃብር በወረደበት ቀን ጥልቅ ምንጮችን ስለ እርሱ በሐዘን ሸፈንኋቸው፤ ወንዞቹን ገታሁ፤ ታላላቅ ፈሳሾችም ተቋረጡ። በእርሱም ምክንያት ሊባኖስን ጨለማ አለበስሁ፤ የደን ዛፎችም ሁሉ ደረቁ።

16. ወደ ጒድጓድ ከሚሄዱት ጋር ወደ መቃብር ባወረድሁት ጊዜ ሲወድቅ በተሰማው ድምፅ አሕዛብ ደነገጡ። ከዚያም የዔድን ዛፎች ሁሉ፣ ምርጥና ልዩ የሆኑት የሊባኖስ ዛፎች፣ ውሃ የጠገቡትም ዛፎች ሁሉ ከምድር በታች ሆነው ተጽናኑ።

17. ከአሕዛብ መካከል ከእርሱ ጋር ያበሩ፣ በጥላው ሥር የኖሩ፣ በሰይፍ ከሞቱት ጋር ለመቀላቀል ወደ መቃብር ወርደዋል።”

18. “ ‘በዔድን ካሉት ዛፎች በውበትና በትልቅነት የሚወዳደርህ የትኛው ነው? ይሁን እንጂ አንተም እንደዚሁ ከዔድን ዛፎች ጋር ከመሬት በታች ትወርዳለህ፤ በሰይፍ ከተገደሉት፣ ካልተገረዙትም መካከል ትጋደማለህ።“ ‘እንግዲህ ፈርዖንና ስፍር ቍጥር የሌለው ሕዝቡ የሚደርስባቸው ይህ ነው፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”