ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ዜና መዋዕል 19:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መንግሥቱ በደኅና በተመለሰ ጊዜ፣

2. ባለ ራእዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው፣ “አንተ ክፉውን መርዳትህና እግዚአብሔርን የሚጠሉትን ማፍቀርህ ተገቢ ነውን? ስለዚህ የእግዚአብሔር ቊጣ ባንተ ላይ ነው፤

3. ይሁን እንጂ የአሼራን ዐምዶች ከምድሪቱ ስላስወገድህና እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልብህን ስላዘጋጀህ፣ መልካም ነገር ተገኝቶብሃል”።

4. ኢዮሣፍጥ በኢየሩሳሌም ተቀመጠ፤ ከቤርሳቤህ እስከ ኰረብታማው አገር እስከ ኤፍሬም ድረስ እንደ ገና በመውጣት ወደ ሕዝቡ መካከል ገብቶ ወደ አባቶቻቸው አምላክ ወደ እግዚአብሔር መለሳቸው።

5. በምድሪቱም ላይ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ዳኞችን ሾመ፤

6. እንዲህም አላቸው፤ “እናንተ የምትፈርዱት ለሰው ሳይሆን፣ ፍርድ በምትሰጡበት ጊዜ ሁሉ ከእናንተ ጋር ለሆነው ለእግዚአብሔር ስለ ሆነ፣ በምትሰጡት ውሳኔ ሁሉ ብርቱ ጥንቃቄ አድርጉ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ዜና መዋዕል 19