ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ነገሥት 3:23-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ስለዚህ፣ “ያ እኮ ደም ነው! ያለ ጥርጥር ነገሥታቱ እርስ በርስ ተዋግተው ተራርደዋል። እንግዲህ ሞዓብ ወደ ምርኮህ ዙር!” ተባባሉ።

24. ሞዓባውያን ወደ እስራኤል ሰፈር ሲወጡም፣ እስራኤላውያን ተነሥተው ወጓቸው፤ ሞዓባውያንም ከፊታቸው ሸሹ። ከዚያም እስራኤላውያን ምድሪቱን ወረው ሞዓባውያንን ፈጇቸው።

25. ከተሞቹን ደመሰሱ፤ መልካሙን የዕርሻ መሬት ሁሉ እስኪሸፍ ነው ድረስ፤ እያንዳንዱ ሰው አንዳንድ ድንጋይ ጣለበት፤ ምንጮቹን በሙሉ ደፈኑ፤ ጥሩ ጥሩውንም ዛፍ ሁሉ ቈርጠው ጣሉ። ቂርሐራሴት ብቻ ከነድንጋይዋ ቀርታ ነበር፤ እርሷም ቢሆን ባለ ወንጭፉ ሰራዊት ከቦ አደጋ ጣለባት።

26. የሞዓባውያን ንጉሥ በጦርነቱ መሸነፉን እንዳወቀ፣ ሰይፍ የታጠቁ ሰባት መቶ ሰዎች ይዞ የኤዶም ንጉሥ ወዳለበት ጥሶ ለመግባት ሞከረ፤ ነገር ግን አልተሳካላቸውም።

27. ከዚያም በእግሩ ተተክቶ የሚነግሠውን፣ የበኵር ልጁን ወስዶ በከተማዪቱ ቅጥር ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበው። በእስራኤልም ላይ ታላቅ ቊጣ ሆነ፤ ከዚያም ለቀው ወደ ገዛ ምድራቸው ተመለሱ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ነገሥት 3