ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ነገሥት 2:17-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. አይሆንም ለማለት ዕፍረት እስኪሰማው ድረስ ግድ አሉት፤ ስለዚህ፣ “በሉ እንግዲያው ላኳቸው” አለ። እነርሱም አምሳ ሰዎች ላኩ፤ ሰዎቹም ሦስት ቀን ሙሉ ፈልገው ሳያገኙት ቀሩ።

18. በኢያሪኮ ቈይቶ ወደ ነበረው ወደ ኤልሳዕ በተመለሱም ጊዜ፣ “ቀድሞውንስ ቢሆን አትሂዱ ብያችሁ አልነበረምን?” አላቸው።

19. የከተማዪቱም ሰዎች ኤልሳዕን፣ “እነሆ ጌታችን፤ እንደምታያት ይህች ከተማ ለኑሮ የተመቸች ናት፤ ይሁን እንጂ ውሃው መጥፎ ሲሆን ምድሪቱም ፍሬ የማትሰጥ ናት” አሉት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ነገሥት 2