ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 4:5-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. የቴቁሔ አባት አሽሑር፣ ሔላና ነዕራ የተባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት።

6. ነዕራም አሑዛምን፣ ኦፌርን፣ ቴምኒን፣ አሐሽታሪን ወለደችለት፤ የነዕራ ዘሮች እነዚህ ነበሩ።

7. የሔላ ወንዶች ልጆች፤ዴሬት፣ ይጽሐር፣ ኤትናን ናቸው።

8. የቆጽ ወንዶች ልጆች ደግሞም ዓኑብ፣ ጾቤባና፣ የሃሩም ናቸው።

9. ያቤጽ ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ሰው ነበረ፤ እናቱም “በጣር የወለድሁት” ስትል ስሙን ያቤጽ አለችው።

10. ያቤጽም፣ “አቤቱ፤ እንድትባርከኝ፣ ግዛቴንም እንድታሰፋልኝ እለምንሃለሁ፤ እጅህ ከእኔ ጋር ትሁን፤ ከሥቃይና ከጒዳትም ጠብቀኝ” በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ጮኸ። እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።

11. የሹሐ ወንድም ክሉብ ምሒርን ወለደ፤ ምሒርም ኤሽቶን ወለደ።

12. ኤሽቶን ቤትራፋንና ፋሴሐን ወለደ፤ የዒር ናሐሽን ከተሞች የቈረቈረ እርሱ ነው። እነዚህ የሬካ ሰዎች ናቸው።

13. የቄኔዝ ወንዶች ልጆች፤ጎቶንያል፣ ሠራያ።የጎቶንያል ወንዶች ልጆች፤ሐታት፣ መዖኖታይ።

14. መዖኖታይ ደግሞ ዖፍራን ወለደ።ሠራያ የኢዮአብ አባት ሲሆን፣ ኢዮአብ ጌሐራሺምን ወለደ፤ የእደ ጥበብ ባለ ሙያዎች ስለ ነበሩ ይህ ስም ተሰጣቸው።

15. የዮፎኔ ልጅ የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ዒሩ፣ ኤላ፣ ነዓም።የኤላ ልጅ፤ቄኔዝ።

16. የይሃሌልኤል ወንዶች ልጆች፤ዚፍ፣ ዚፋ፣ ቲርያ፣ አሣርኤል።

17. የዕዝራ ወንዶች ልጆች፤ዬቴር፣ ሜሬድ፣ ዔፌር፣ ያሎን። ከሜሬድ ሚስቶች አንዲቱ ማርያምን፣ ሸማይንና የኤሽትምዓን አባት ይሽባን ወለደች።

18. አይሁዳዊት ሚስቱም የጌዶርን አባት ዮሬድን፣ የሦኮን አባት ሔቤርን፣ የዛኖዋን አባት ይቁቲኤልን ወለደች፤ እነዚህም ሜሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው።

19. የሆዲያ ሚስት የነሐም እኅት ወንዶች ልጆች፤የገርሚው የቅዒላ አባት፣ ማዕካታዊው ኤሽትሞዓ።

20. የሺሞን ወንዶች ልጆች፤አምኖን፣ ሪና፣ ቤንሐናን፣ ቲሎን። የይሺዒ ዘሮች፤ ዞሔትና ቤንዞሔት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 4