ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 14:9-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን መጥተው የራፋይምን ሸለቆ ወረሩ።

10. ስለዚህ ዳዊት፣ “ወጥቼ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ልጣልን? አንተስ በእጄ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፣ “አዎን ውጣ! በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ” ብሎ መለሰለት።

11. ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ በኣልፐራሲም ወጡ፤ በዚያም ድል አደረጋቸው። ዳዊትም፣“ውሃ ነድሎ እንደሚወጣ ሁሉ እግዚአብሔርም ጠላቶቼን በእጄ አፈረሳቸው” አለ፤ ከዚህም የተነሣ ያን ቦታ “በኣልፐራሲም” ብለው ሰየሙት።

12. ፍልስጥኤማውያን አማልክቶቻቸውን በዚያው ጥለዋቸው ስለ ነበር፣ ዳዊት በእሳት እንዲያቃጥሏቸው አዘዘ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 14