ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዕብራውያን 10:16-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. “ከዚያም በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው፤ይላል ጌታ፤ሕጌን በልባቸው አኖራለሁ፤በአእምሮአቸውም እጽፈዋለሁ።”

17. ደግሞም፣“ኀጢአታቸውንና ዐመፃቸውን፣ከእንግዲህ አላስብም” ይላል።

18. እነዚህ ይቅር ከተባሉ በኋላ ከእንግዲህ ስለ ኀጢአት የሚቀርብ መሥዋዕት አይኖርም።

19. እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ በኢየሱስ ደም ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት ድፍረት አግኝተናል፤

20. ይኸውም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል በከፈተልን አዲስና ሕያው መንገድ ነው።

21. በእግዚአብሔር ቤት ላይ የተሾመ ታላቅ ሊቀ ካህናት ስላለን

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዕብራውያን 10