ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዕብራውያን 10:15-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. መንፈስ ቅዱስም ስለዚህ ነገር ይመሰክርልናል፤ በመጀመሪያ እንዲህ ይላል፤

16. “ከዚያም በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው፤ይላል ጌታ፤ሕጌን በልባቸው አኖራለሁ፤በአእምሮአቸውም እጽፈዋለሁ።”

17. ደግሞም፣“ኀጢአታቸውንና ዐመፃቸውን፣ከእንግዲህ አላስብም” ይላል።

18. እነዚህ ይቅር ከተባሉ በኋላ ከእንግዲህ ስለ ኀጢአት የሚቀርብ መሥዋዕት አይኖርም።

19. እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ በኢየሱስ ደም ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት ድፍረት አግኝተናል፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዕብራውያን 10