ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሮሜ 16:19-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. የእናንተን ታዛዥነት ሁሉም ሰምተዋል፤ በዚህም እኔ እጅግ ተደስቻለሁ። ሆኖም በጎ ስለ ሆነው ነገር ጥበበኞች፣ ክፉ ስለ ሆነውም የዋሆች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ።

20. የሰላም አምላክ፣ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል።የጌታችን የኢየሱስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።

21. አብሮኝ የሚሠራው ጢሞቴዎስ፣ እንዲሁም ዘመዶቼ የሆኑት ሉቂዮስ፣ ኢያሶንና ሱሲጴጥሮስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

22. ይህን መልእክት የጻፍሁ እኔ ጤርጥዮስ፣ በጌታ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሮሜ 16