ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማርቆስ 9:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. እጅግ ስለ ፈሩ የሚናገረውን አያውቅም ነበር።

7. ከዚያም ደመና መጥቶ ጋረዳቸው፤ ከደመናውም ውስጥ፣ “ይህ የምወደው ልጄ ነው፤ እርሱን ስሙት!” የሚል ድምፅ መጣ።

8. ወዲያውም ዙሪያቸውን ሲመለከቱ ከኢየሱስ በቀር ማንም አብሮአቸው አልነበረም።

9. ከተራራው ላይ በሚወርዱበትም ጊዜ፣ የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያዩትን ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው።

10. እነርሱም የተናገራቸውን ቃል በልባቸው አሳደሩት፤ ነገር ግን፣ “ከሙታን መነሣት” ምን ማለት እንደሆነ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማርቆስ 9