ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማርቆስ 10:49-52 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

49. ኢየሱስም ቆም ብሎ፣ “ጥሩት” አላቸው።እነርሱም ዐይነ ስውሩን፣ “አይዞህ፤ ተነሥ፤ ይጠራሃል!” አሉት።

50. እርሱም ልብሱን ጥሎ ብድግ በማለት፣ ተነሥቶ ወደ ኢየሱስ መጣ።

51. ኢየሱስም፣ “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” አለው።ዐይነ ስውሩም፣ “መምህር ሆይ፤ እንዳይ እፈልጋለሁ” አለው።

52. ኢየሱስም፣ “ሂድ፣ እምነትህ አድኖሃል” አለው፤ ወዲያውም ዐይኑ በራለት፤ በመንገድም ኢየሱስን ተከትሎት ሄደ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማርቆስ 10