ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሐዋርያት ሥራ 27:29-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

29. ከቋጥኞቹም ጋር እንዳንላተም በመፍራት፣ አራት መልሕቆች ከመርከቡ በስተ ኋላ ጣሉ፤ ምነው በነጋ እያሉም ይለምኑ ነበር።

30. መርከበኞቹም ከመርከቡ በስተ ፊት መልሕቅ የሚጥሉ መስለው፣ ትንሿን ጀልባ በማውረድ ከመርከቧ ሊያመልጡ ሞከሩ።

31. ጳውሎስም የመቶ አለቃውንና ወታደሮቹን፣ “እነዚህ ሰዎች መርከቡ ላይ ካልቈዩ እናንተም ልትተርፉ አትችሉም” አላቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሐዋርያት ሥራ 27