ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሐዋርያት ሥራ 26:28-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. አግሪጳም ጳውሎስን፣ “እንዲህ በቀላሉ ክርስቲያን የምታደርገኝ ይመስልሃልን?” አለው።

29. ጳውሎስም፣ “በቀላሉም ሆነ በብዙ፣ አንተ ብቻ ሳትሆን ዛሬ የሚሰሙኝ ሁሉ፣ ከዚህ ከታሰርሁበት ሰንሰለት በስተቀር፣ እንደ እኔ ይሆኑ ዘንድ እግዚአብሔርን እለምናለሁ” አለ።

30. ከዚህ በኋላ ንጉሡም፣ አገረ ገዡም፣ በርኒቄም፣ ከእነርሱ ጋር የተቀመጡትም ተነሡ፤

31. ወጥተውም ሲሄዱ፣ “ይህ ሰው እንኳን ለሞት ለእስራት የሚያበቃው ነገር አላደረገም” ተባባሉ።

32. አግሪጳም ፊስጦስን፣ “ይህ ሰው ወደ ቄሳር ይግባኝ ባይል ኖሮ መልቀቅ ይቻል ነበር” አለው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሐዋርያት ሥራ 26