ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሉቃስ 3:2-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ሐናና ቀያፋም ሊቃነ ካህናት ሳሉ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ ልጅ ወደ ዮሐንስ በምድረ በዳ መጣ።

3. እርሱም ለኀጢአት ስርየት የሚሆን የንስሓን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ወንዝ አካባቢ ወዳሉት ስፍራዎች ሁሉ መጣ፤

4. ይኸውም ነቢዩ ኢሳይያስ በመጽሐፉ እንዲህ ሲል በጻፈው ቃል መሠረት ነበር፤“በበረሓ እንዲህ ብሎ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፤‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ጐዳናውንም አቅኑ፤

5. ሸለቆው ሁሉ ይሞላል፤ተራራውና ኰረብታው ሁሉ ዝቅ ይላል፤ጠማማው መንገድ ቀና፣ሸካራውም ጐዳና ትክክል ይሆናል፤

6. የሰውም ዘር ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ያያል።’ ”

7. ዮሐንስም በእርሱ እጅ ሊጠመቁ የወጡትን ሰዎች እንዲህ ይላቸው ነበር፤ “እናንት የእፉኝት ልጆች፣ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን መከራችሁ?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሉቃስ 3