ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሉቃስ 21:13-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ይህም ለመመስከር ጥሩ ዕድል ይሆንላችኋል።

14. ስለዚህ ምን መልስ እንሰጣለን በማለት አስቀድማችሁ እንዳትጨነቁ ይህን ልብ በሉ፤

15. ተቃዋሚዎቻችሁ ሁሉ ሊቋቋሙትና ሊያስተባብሉት የማይችሉትን ቃልና ጥበብ እሰጣችኋለሁና።

16. ወላጆቻችሁ፣ ወንድሞቻችሁ፣ ዘመዶቻችሁና ጓደኞቻችሁ እንኳ ሳይቀሩ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ከእናንተም አንዳንዶቹን ይገድላሉ፤

17. ስለ ስሜም በሰዎች ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።

18. ነገር ግን ከራሳችሁ ጠጒር አንዷ እንኳ አትጠፋም፤

19. ጸንታችሁም በመቆም ነፍሳችሁን ታተርፋላችሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሉቃስ 21