ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሉቃስ 14:27-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. የራሱንም መስቀል ተሸክሞ የማይከተለኝ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።

28. “ከእናንተ አንድ ሰው ሕንጻ ለመሥራት ቢፈልግ፣ መደምደም መቻል አለመቻሉን በመጀመሪያ ተቀምጦ ዋጋውን የማይተምን ማን ነው?

29. መሠረቱን ጥሎ መደምደም ቢያቅተው፣ ያዩት ሁሉ ይዘባበቱበታል፤

30. እንዲህም ይላሉ፤ ‘ይህ ሰው ማነጽ ጀምሮ ነበር፤ መደምደም ግን አቃተው።’

31. “ወይም አንድ ንጉሥ ከሌላው ንጉሥ ጋር ጦርነት ሊገጥም በሚነሣበት ጊዜ፣ ሃያ ሺህ ሰራዊት አስከትቶ የሚመጣበትን ንጉሥ፣ በዐሥር ሺህ ሰራዊት መመከት እንደሚችል ተቀምጦ የማይመክር ማን ነው?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሉቃስ 14