ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ተሰሎንቄ 5:18-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. በማናቸውም ሁኔታ አመስግኑ፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ይህ ነውና።

19. የመንፈስን እሳት አታዳፍኑ፤

20. ትንቢትን አትናቁ።

21. ሁሉን ነገር ፈትኑ፤ መልካም የሆነውን ያዙ፤

22. ከማናቸውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ።

23. የሰላም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁ፣ ነፍሳችሁና ሥጋችሁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ ያለ ነቀፋ ይጠበቁ።

24. የጠራችሁ የታመነ ነው፤ እርሱም ያደርገዋል።

25. ወንድሞች ሆይ፤ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ተሰሎንቄ 5