ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ተሰሎንቄ 5:13-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ስለ ሥራቸውም በፍቅር እጅግ አክብሯቸው። እርስ በርሳችሁም በሰላም ኑሩ።

14. ወንድሞች ሆይ፤ ይህን እንመክራችኋለን፤ ሥራ ፈቶችን ገሥጿቸው፤ ፈሪዎችን አደፋፍሯቸው፤ ደካሞችን እርዷቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።

15. ማንም በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን እርስ በርሳችሁም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ሁል ጊዜ መልካም የሆነውን ነገር ለማድረግ ተጣጣሩ።

16. ሁል ጊዜ ደስ ይበላችሁ፤

17. ሳታቋርጡ ጸልዩ፤

18. በማናቸውም ሁኔታ አመስግኑ፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ይህ ነውና።

19. የመንፈስን እሳት አታዳፍኑ፤

20. ትንቢትን አትናቁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ተሰሎንቄ 5