ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ቆሮንቶስ 9:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ወይስ ጥረን ግረን መኖር ያለብን እኔና በርናባስ ብቻ ነን?

7. ለመሆኑ በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል ማን ነው? ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? መንጋ እየጠበቀ የከብቱን ወተት የማይጠጣ ማን ነው?

8. ይህን የምናገረው እንደ ሰው አስተሳሰብ ነውን? የኦሪትስ ሕግ ይህንኑ ይል የለምን?

9. በሙሴ ሕግ፣ “የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር” ተብሎ ተጽፎአልና። ለመሆኑ፣ እግዚአብሔርን ያሳሰበው የበሬ ጒዳይ ነውን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ቆሮንቶስ 9