ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ቆሮንቶስ 9:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እኔ ነጻ ሰው አይደለሁምን? ሐዋርያስ አይደለሁምን? ጌታችንን ኢየሱስን አላየሁትምን? እናንተስ በጌታ የድካሜ ፍሬዎች አይደላችሁምን?

2. ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን እንኳ ለእናንተ ግን በርግጥ ሐዋርያ ነኝ፤ ምክንያቱም በጌታ የሐዋርያነቴ ማኅተም እናንተ ናችሁ።

3. ለሚመረምሩኝ የምሰጠው መልስ ይህ ነው።

4. ለመሆኑ፣ የመብላትና የመጠጣት መብት የለንምን?

5. እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት፣ እንደ ጌታ ወንድሞችና እንደ ኬፋ ሁሉ፣ እኛስ አማኝ ሚስት ይዘን የመዞር መብት የለንምን?

6. ወይስ ጥረን ግረን መኖር ያለብን እኔና በርናባስ ብቻ ነን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ቆሮንቶስ 9