ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ቆሮንቶስ 9:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እኔ ነጻ ሰው አይደለሁምን? ሐዋርያስ አይደለሁምን? ጌታችንን ኢየሱስን አላየሁትምን? እናንተስ በጌታ የድካሜ ፍሬዎች አይደላችሁምን?

2. ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን እንኳ ለእናንተ ግን በርግጥ ሐዋርያ ነኝ፤ ምክንያቱም በጌታ የሐዋርያነቴ ማኅተም እናንተ ናችሁ።

3. ለሚመረምሩኝ የምሰጠው መልስ ይህ ነው።

4. ለመሆኑ፣ የመብላትና የመጠጣት መብት የለንምን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ቆሮንቶስ 9