ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ቆሮንቶስ 6:2-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ቅዱሳን በዓለም ላይ እንደሚፈርዱ አታውቁምን? በዓለም ላይ የምትፈርዱ ከሆነ፣ እንግዲያው፣ በትንሹ ነገር ላይ ለመፍረድ አትበቁምን?

3. በምድራዊ ሕይወት ጒዳይ ቀርቶ፣ በመላእክት ላይ እንኳ እንደምንፈርድ አታውቁምን?

4. እንግዲህ እንዲህ ያለ ጒዳይ ሲያጋጥ ማችሁ፣ በቤተ ክርስቲያን የተናቁትን ሰዎች ፈራጅ አድርጋችሁ ሹሟ!

5. ይህንንም የምለው ላሳፍራችሁ ብዬ ነው። ለመሆኑ ከመካካላችሁ ወንድሞችን ለማስታረቅ የሚበቃ አስተዋይ ሰው የለምን?

6. ነገር ግን ወንድም ወንድሙን ለመክሰስ ፍርድ ቤት ይሄዳል፤ ያውም በማያምኑ ሰዎች ፊት!

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ቆሮንቶስ 6