ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ቆሮንቶስ 5:4-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. በምትሰበሰቡበት ጊዜ እኔም በመንፈስ ከእናንተ ጋር ስለ ምሆን፣ በጌታችን በኢየሱስ ስምና በመካከላችሁ በሚገኘው በጌታችን በኢየሱስ ኀይል፣

5. ሥጋው ጠፍቶ መንፈሱ በጌታ ቀን ትድን ዘንድ፣ እንደዚህ ዐይነቱ ለሰይጣን ይሰጥ።

6. መመካታችሁ መልካም አይደለም። ጥቂት እርሾ ብዙውን ሊጥ እንደሚያቦካው አታውቁምን?

7. አሁን ያለ እርሾ እንደሆናችሁ ሁሉ አዲስ ሊጥ እንድትሆኑ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ፤ የፋሲካ በጋችን የሆነው ክርስቶስ ተሠውቶአልና።

8. ስለዚህ በዓሉን ግፍና ክፋት በሞላበት እርሾ፣ በአሮጌ እርሾ ሳይሆን፣ እርሾ በሌለበት ቂጣ በቅንነትና በእውነት እናክብር።

9. ከሴሰኞች ጋር እንዳትተባበሩ በመልእክቴ ጽፌላችሁ ነበር፤

10. እንዲህም ስል በጠቅላላው ከዚህ ዓለም ሴሰኞች ወይም ስግብ ግቦችና ቀማኞች፣ ወይም ከጣዖት አምላኪዎች ጋር አትተባበሩ ለማለት አይደለም፤ እንደዚያማ ቢሆን ከዚህ ዓለም ጨርሶ መለየት ያስፈልጋችሁ ነበር።

11. ነገር ግን አሁን የጻፍሁላችሁ፣ “ወንድም ነኝ” እያለ ከሚሴስን ወይም ከሚስገበገብ ወይም ጣዖትን ከሚያመልክ ወይም ከሚሳደብ ወይም ከሚሰክር ወይም ከሚቀማ ጋር እንዳትተባበሩ ነው፤ ከእንደዚህ ዐይነቱ ሰው ጋር ምግብ እንኳ አትብሉ።

12. ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ባሉት ሰዎች ላይ ለመፍረድ እኔን ምን አገባኝ? በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉት ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱምን?

13. ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ባሉት ላይ የሚፈርድ ግን እግዚአብሔር ነው፤ እንግዲህ፣ “ክፉውን ሰው ከመካከላችሁ አስወግዱት።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ቆሮንቶስ 5