ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 5:28-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. ላሜሕ፣ ዕድሜው 182 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ ልጅ ወለደ።

29. ስሙንም “እግዚአብሔር (አዶናይ) በረገማት ምድር ከልፋታችንና ከጒልበታችን ድካም ያሳርፈናል” ሲል ኖኅ ብሎ ጠራው።

30. ላሜሕ ኖኅን ከወለደ በኋላ፣ 595 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

31. ላሜሕ በአጠቃላይ 777 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

32. ኖኅ ዕድሜው 500 ዓመት ሲሆን ሴምን፣ ካምንና ያፌትን ወለደ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 5