ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40
  41. 41
  42. 42
  43. 43
  44. 44
  45. 45
  46. 46
  47. 47
  48. 48
  49. 49
  50. 50

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከአዳም እስከ ኖኅ

1. የአዳም የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው ነው፦እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሰውን ሲፈጥረው በራሱ አምሳል አበጀው፤

2. ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፤ ባረካቸው፤ በተፈጠሩም ጊዜ “ሰው” ብሎ ጠራቸው።

3. አዳም፣ ዕድሜው 130 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እርሱን ራሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፤ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው።

4. ሴት ሄኖስን ከወለደ በኋላ አዳም 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤

5. አዳም በአጠቃላይ 930 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

6. ሴት፣ ዕድሜው 105 ዓመት ሲሆን ሄኖስን ወለደ፤

7. ሴት ሄኖስን ከወለደ በኋላ 807 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

8. ሴት በአጠቃላይ 912 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

9. ሄኖስ፣ ዕድሜው 90 ዓመት በሆነ ጊዜ ቃይናንን ወለደ፤

10. ሄኖስ ቃይናንን ከወለደ በኋላ 815 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

11. ሄኖስ በአጠቃላይ 905 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

12. ቃይናን፣ ዕድሜው 70 ዓመት ሲሆን መላልኤልን ወለደ፤

13. ቃይናን መላልኤልን ከወለደ በኋላ 840 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

14. ቃይናን በአጠቃላይ 910 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

15. መላልኤል፣ ዕድሜው 65 ዓመት በሆነ ጊዜ ያሬድን ወለደ፤

16. መላልኤል ያሬድን ከወለደ በኋላ 830 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

17. መላልኤል በአጠቃላይ 895 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

18. ያሬድ፣ ዕድሜው 162 ዓመት ሲሆን ሄኖክን ወለደ፤

19. ያሬድ ሄኖክን ከወለደ በኋላ 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

20. ያሬድ በአጠቃላይ 962 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

21. ሄኖክ፣ ዕድሜው 65 ዓመት በሆነ ጊዜ ማቱሳላን ወለደ፤

22. ሄኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ አካሄዱን ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ጋር በማድረግ 300 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

23. ሄኖክ በአጠቃላይ 365 ዓመት ኖረ፤

24. ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ጋር አደረገ፤ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ስለ ወሰደውም አልተገኘም።

25. ማቱሳላ፣ ዕድሜው 187 ዓመት ሲሆን ላሜሕን ወለደ፤

26. ማቱሳላ ላሜሕን ከወለደ በኋላ፣ 782 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤

27. ማቱሳላ በአጠቃላይ 969 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

28. ላሜሕ፣ ዕድሜው 182 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ ልጅ ወለደ።

29. ስሙንም “እግዚአብሔር (አዶናይ) በረገማት ምድር ከልፋታችንና ከጒልበታችን ድካም ያሳርፈናል” ሲል ኖኅ ብሎ ጠራው።

30. ላሜሕ ኖኅን ከወለደ በኋላ፣ 595 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

31. ላሜሕ በአጠቃላይ 777 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

32. ኖኅ ዕድሜው 500 ዓመት ሲሆን ሴምን፣ ካምንና ያፌትን ወለደ።