ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 5:22-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. ሄኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ አካሄዱን ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ጋር በማድረግ 300 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

23. ሄኖክ በአጠቃላይ 365 ዓመት ኖረ፤

24. ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ጋር አደረገ፤ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ስለ ወሰደውም አልተገኘም።

25. ማቱሳላ፣ ዕድሜው 187 ዓመት ሲሆን ላሜሕን ወለደ፤

26. ማቱሳላ ላሜሕን ከወለደ በኋላ፣ 782 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤

27. ማቱሳላ በአጠቃላይ 969 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

28. ላሜሕ፣ ዕድሜው 182 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ ልጅ ወለደ።

29. ስሙንም “እግዚአብሔር (አዶናይ) በረገማት ምድር ከልፋታችንና ከጒልበታችን ድካም ያሳርፈናል” ሲል ኖኅ ብሎ ጠራው።

30. ላሜሕ ኖኅን ከወለደ በኋላ፣ 595 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

31. ላሜሕ በአጠቃላይ 777 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

32. ኖኅ ዕድሜው 500 ዓመት ሲሆን ሴምን፣ ካምንና ያፌትን ወለደ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 5