ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 5:21-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. ሄኖክ፣ ዕድሜው 65 ዓመት በሆነ ጊዜ ማቱሳላን ወለደ፤

22. ሄኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ አካሄዱን ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ጋር በማድረግ 300 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

23. ሄኖክ በአጠቃላይ 365 ዓመት ኖረ፤

24. ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ጋር አደረገ፤ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ስለ ወሰደውም አልተገኘም።

25. ማቱሳላ፣ ዕድሜው 187 ዓመት ሲሆን ላሜሕን ወለደ፤

26. ማቱሳላ ላሜሕን ከወለደ በኋላ፣ 782 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤

27. ማቱሳላ በአጠቃላይ 969 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 5