ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 5:17-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. መላልኤል በአጠቃላይ 895 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

18. ያሬድ፣ ዕድሜው 162 ዓመት ሲሆን ሄኖክን ወለደ፤

19. ያሬድ ሄኖክን ከወለደ በኋላ 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

20. ያሬድ በአጠቃላይ 962 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

21. ሄኖክ፣ ዕድሜው 65 ዓመት በሆነ ጊዜ ማቱሳላን ወለደ፤

22. ሄኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ አካሄዱን ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ጋር በማድረግ 300 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

23. ሄኖክ በአጠቃላይ 365 ዓመት ኖረ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 5