ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 46:5-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሣ፤ የእስራኤል ወንዶች ልጆችም አባታቸውን ያዕቆብን፣ ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ፈርዖን ለያዕቆብ በላካቸው ሠረገላዎች ላይ አወጧቸው።

6. ከብቶቻቸውንና በከነዓን ምድር ያፈሩትን ሀብት ንብረታቸውን ይዘው፣ ያዕቆብና ዘሮቹ በሙሉ ወደ ግብፅ ወረዱ።

7. ወደ ግብፅም የወረደው፣ ወንዶች ልጆቹንና ወንዶች የልጅ ልጆቹን፣ ሴቶች ልጆቹንና ሴቶች የልጅ ልጆቹን ማለት ዘሮቹን ሁሉ ይዞ ነው።

8. ወደ ግብፅ የወረዱት የእስራኤል ልጆች፣ ያዕቆብ ዘሮቹ እነዚህ ናቸው፦የያዕቆብ የበኵር ልጅ ሮቤል።

9. የሮቤል ልጆች፦ሄኖኅ፣ ፈሉሶ፣ አስሮን እና ከርሚ ናቸው።

10. የስምዖን ልጆች፦ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ጾሐርና ከከነዓናዊቷ ሴት የተወለደውሳኡል ናቸው።

11. የሌዊ ልጆች፦ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው።

12. የይሁዳ ልጆች፦ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፣ ፋሬስ እናዛራ ናቸው። ነገር ግን ዔርና አውናንበከነዓን ምድር ሞቱ።

13. የይሳኮር ልጆች፦ቶላ፣ ፉዋ፣ ዮብና ሺምሮን ናቸው፤

14. የዛብሎን ልጆች፦ሴሬድ፣ ኤሎንና ያሕልኤል ናቸው፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 46