ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 46:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እስራኤልም ጓዙን ሁሉ ጠቅልሎ ተነሣ፤ ቤርሳቤህም ሲደርስ፣ ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ (ኤሎሂም) መሥዋዕት ሠዋ።

2. እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) ሌሊት በራእይ ለእስራኤል ተገልጦ “ያዕቆብ፣ ያዕቆብ” ብሎ ጠራው። እርሱም፣ “እነሆ፣ አለሁ” አለ።

3. እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ አምላክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ነኝ፤ ወደ ግብፅ ለመውረድ አትፍራ፤ በዚያ ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና፤

4. አብሬህ ወደ ግብፅ እወርዳለሁ፤ ከዚያም መልሼ አወጣሃለሁ፤ የዮሴፍ የራሱ እጆችም ዐይኖችህን ይገጥሟቸዋል።”

5. ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሣ፤ የእስራኤል ወንዶች ልጆችም አባታቸውን ያዕቆብን፣ ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ፈርዖን ለያዕቆብ በላካቸው ሠረገላዎች ላይ አወጧቸው።

6. ከብቶቻቸውንና በከነዓን ምድር ያፈሩትን ሀብት ንብረታቸውን ይዘው፣ ያዕቆብና ዘሮቹ በሙሉ ወደ ግብፅ ወረዱ።

7. ወደ ግብፅም የወረደው፣ ወንዶች ልጆቹንና ወንዶች የልጅ ልጆቹን፣ ሴቶች ልጆቹንና ሴቶች የልጅ ልጆቹን ማለት ዘሮቹን ሁሉ ይዞ ነው።

8. ወደ ግብፅ የወረዱት የእስራኤል ልጆች፣ ያዕቆብ ዘሮቹ እነዚህ ናቸው፦የያዕቆብ የበኵር ልጅ ሮቤል።

9. የሮቤል ልጆች፦ሄኖኅ፣ ፈሉሶ፣ አስሮን እና ከርሚ ናቸው።

10. የስምዖን ልጆች፦ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ጾሐርና ከከነዓናዊቷ ሴት የተወለደውሳኡል ናቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 46