ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 11:26-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. ታራ 70 ዓመት ከሆነው በኋላ አብራምን፣ ናኮርንና ሐራንን ወለደ።

27. የታራ ትውልድ ይህ ነው፦ታራ፣ አብራምን ናኮርንና ሐራንን ወለደ፤ሐራንም ሎጥን ወለደ።

28. ሐራን፣ አባቱ ታራ ገና በሕይወት እንዳለ በከለዳውያን ምድር በምትገኘው በተወለደባት ከተማ በዑር ሞተ።

29. አብራምና ናኮር ሁለቱም ሚስት አገቡ፤ የአብራም ሚስት ሦራ ስትባል፣ የናኮር ሚስት ደግሞ ሚልካ ትባል ነበር፤ ሚልካም የሐራን ልጅ ናት፤ ሐራንም የሚልካና የዮስካ አባት ነበረ።

30. ሦራ መካን ነበረች፤ ልጅ አልነበራትም።

31. ታራ ልጁን አብራምን፣ ሐራን የወለደውን የልጅ ልጁን ሎጥን እንዲሁም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ይዞ ወደ ከነዓን ለመሄድ በከለዳውያን ምድር ከምትገኘው ከዑር አብረው ወጡ፤ ነገር ግን ካራን በደረሱ ጊዜ በዚያ ተቀመጡ።

32. ታራ 205 ዓመት ኖሮ በካራን ሞተ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 11