ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 10:22-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. የሴም ልጆች፦ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ናቸው።

23. የአራም ልጆች፦ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሶሕ ናቸው።

24. አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤ሳላም ዔቦርን ወለደ።

25. ለዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤አንደኛው ልጅ በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለ ነበር ፍሌቅ ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።

26. ዮቅጣንም፦ የኤልሞሳድ፣ የሣሌፍ፣ የሐስረ ሞት፣ የያራሕ፣

27. የሀደራም፣ የአውዛል፣ የደቅላ አባት ነበረ፤

28. እንዲሁም የዖባል፣ የአቢማኤል፣ የሳባ፣

29. የኦፊር፣ የኤውላጥ፣ የዮባል አባት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው።

30. መኖሪያ ስፍራቸውም እስከ ሶፋር ድረስ ይዘልቃል።

31. እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የሴም ዝርያዎች ናቸው።

32. የኖኅ ወንዶች ልጆች ጐሣዎች እንደ ትውልዳቸው በየነገዳቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውሃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ የተሠራጩት ከእነዚሁ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 10