ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 10:2-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. የያፌት ልጆች፦ጋሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሞሳሕ፣ ቴራስ ናቸው።

3. የጋሜር ልጆች፦አስከናዝ፣ ራፋት፣ ቴርጋማ ናቸው።

4. የያዋን ልጆች፦ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም፣ ሮዲኢ ናቸው።

5. ከእነዚህም በየነገዳቸው፣ በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች፣ በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ።

6. የካም ልጆች፦ኩሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥ፣ ከነዓን ናቸው።

7. የኩሽ ልጆች፦ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማ፣ ሰበቅታ ናቸው።የራዕማ ልጆች፦ሳባ፣ ድዳን ናቸው።

8. ኩሽ የናምሩድ አባት ነበረ፤ ናምሩድም በምድር ላይ ኀያል ሰው እየሆነ ሄደ።

9. በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ብርቱ አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም፣ “በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት እንደ ናምሩድ ብርቱ አዳኝ” ይባል ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 10