ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 10:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የኖኅ ልጆች የሴም፣ የካምና የያፌት ትውልድ ይህ ነው፤ እነርሱም ራሳቸው ከጥፋት ውሃ በኋላ ወንዶች ልጆችን ወለዱ።

2. የያፌት ልጆች፦ጋሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሞሳሕ፣ ቴራስ ናቸው።

3. የጋሜር ልጆች፦አስከናዝ፣ ራፋት፣ ቴርጋማ ናቸው።

4. የያዋን ልጆች፦ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም፣ ሮዲኢ ናቸው።

5. ከእነዚህም በየነገዳቸው፣ በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች፣ በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ።

6. የካም ልጆች፦ኩሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥ፣ ከነዓን ናቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 10