ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 9:32-35 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

32. ስንዴውና አጃው ግን በዚያ ወቅት ባለማፍራቱ አልጠፋም ነበር።

33. ከዚያም ሙሴ ከፈርዖን ተለይቶ ከከተማው ወጣ። እጁን ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ዘረጋ፤ ነጎድጓዱና በረዶው ቆመ፤ ዝናቡም በምድሪቱ ላይ መዝነቡን አቆመ።

34. ፈርዖንም ዝናቡ፣ በረዶውና ነጎድጓዱ መቆሙን ባየ ጊዜ እንደ ገና በደለ፤ እርሱና ሹማምቶቹ ልባቸውን አደነደኑ።

35. ስለዚህ የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ እንደ ተናገረውም እስራኤላውያን ይሄዱ ዘንድ አልለቀቃቸውም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 9