ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 8:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን አለው፤ “ወደ ፈርዖን ዘንድ ሄደህ፣ እንዲህ በለው፤ ‘እግዚአብሔር (ያህዌ) የሚለው ይህ ነው፤ “እኔን ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።

2. እነርሱን ለመልቀቅ እምቢ ብትል አገርህን ሁሉ በጓጒንቸር መቅሠፍት እመታዋለሁ።

3. አባይ በጓጒንቸሮች ይሞላል፤ ወጥተውም ወደ ቤተ መንግሥትህና ወደ መኝታ ክፍልህ፣ ወደ አልጋህም ወደ ሹማምቶችህና ወደ ሕዝብህ ቤቶች፣ ወደ ምድጆችህና ወደ ቡሃቃዎችህ ይገባሉ።

4. ጓጒንቸሮቹ ወደ አንተና ወደ ሕዝብህ ወደ ሹማምቶችህም ሁሉ ይመጡባችኋል።’ ”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 8