ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 4:26-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. ስለዚህም እግዚአብሔር (ያህዌ) ተወው፤ “አንተ የደም ሙሽራ ነህ” ያለችው በግርዛቱ ምክንያት ነው።

27. እግዚአብሔር (ያህዌ) አሮንን፣ “ሙሴን እንድታገኘው ወደ ምድረ በዳ ሂድ” አለው። እርሱም ሙሴን በእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ተራራ አገኘው፤ ሳመውም።

28. ሙሴም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲናገር የላከውን ቃል በሙሉና እንዲፈጽማቸው ስላዘዘው ታምራዊ ምልክቶች ሁሉ ለአሮን ነገረው።

29. ሙሴና አሮን ሄዱና የእስራኤልን ሕዝብ አለቆች በአንድነት ሰበሰቡ፤

30. አሮንም እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ የነገረውን ቃል በሙሉ ነገራቸው። ታምራቱንም በሕዝቡ ፊት አደረገ።

31. ሕዝቡም አመኑ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ስለ እነርሱ የሚገደው መሆኑንና መከራቸውን ማየቱን በሰሙ ጊዜ ተንበረከኩ፤ በስግደትም አመለኩት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 4