ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 27:12-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. “የአደባባዩ ምዕራብ ጫፍ ስፋቱ አምሳ ክንድ ሆኖ ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር መቆሚያዎች ያሉት መጋረጃዎች ይኑሩት።

13. በምሥራቅ ጫፍ በፀሓይ መውጫ በኩል ያለው አደባባይ አሁንም አምስት ክንድ ስፋት ይኑረው።

14. ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው ርዝመታቸው ዐሥራ አምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎች በአንድ በኩል ባለው ደጃፍ ይሁኑ።

15. ሦስት ምሰሶዎች ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው ርዝመታቸው ዐሥራ አምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎች በሌላው በኩል ይሁኑ።

16. “ለአደባባዩ መግቢያ አራት ምሰሶዎችና አራት መቆሚያዎች ያሉት ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከቀጭን በፍታ የተፈተለ፣ ጥልፍ ጠላፊ የጠለፈበት ሃያ ክንድ ርዝመት ያለው መጋረጃ ይሁን።

17. በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎች፣ ኵላቦችና የነሐስ መቆሚያዎች ይኑሯቸው።

18. አደባባዩ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ፣ ስፋቱ አምሳ ክንድ ሆኖ፣ በቀጭኑ ከተፈተለ ማግ ቁመታቸው አምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎችና የነሐስም መቆሚያዎች ያሉት ይሁን።

19. ጥቅማቸው ምንም ዐይነት ይሁን፣ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በሙሉ የድንኳኑና የአደባባዩ ካስማዎችም ሁሉ ሳይቀሩ ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 27