ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 34:9-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ሙሴ እጆቹን ጭኖበት ነበርና፣ የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ መንፈስ ተሞላ። ስለዚህ እስራኤላውያን አደመጡት፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን አዞት የነበረውንም ሁሉ አደረጉ።

10. እግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ለፊት ያወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል አልተነሣም።

11. እግዚአብሔር (ያህዌ) ልኮት፣ እነዚያን ታምራዊ ምልክቶችና ድንቆች ሁሉ በግብፅ በፈርዖን፣ በሹማምቱና በምድሪቱ ሁሉ ላይ እንዲያደርግ የላከውን ያደረገ ማንም ሰው አልነበረም።

12. ሙሴ በእስራኤል ሁሉ ፊት ያሳየውን ታላቅ ኀይል ያሳየ ወይም ያደረገውን አስፈሪ ተግባር የፈጸመ ማንም ሰው የለም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘዳግም 34