ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 26:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፣ ስትወርሳትና ስትኖርባት፣

2. አምላክህእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰ በስበው ሰብል ሁሉ፣ በኵራት ወስደህ በቅርጫት ውስጥ አድርገው፤ ከዚያም አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ ሂድ፤

3. በዚያም ወቅት ለሚያገለግለው ካህን፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ለእኛ ሊሰጠን ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር እንደ ገባሁ ዛሬ በአምላክህበእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት እናገራለሁ” በለው።

4. ካህኑም ቅርጫቱን ከእጅህ ተቀብሎ፣ በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) መሠዊያ ፊት ለፊት ያስቀምጠዋል።

5. አንተም በአምላክህ በእግዚአብሔር (ያህዌ ኤሎሂም) ፊት እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፤ “አባቴ ዘላን ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚያም ተቀመጠ፤ ታላቅ፣ ኀያልና ቊጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ።

6. ግብፃውያን ግን ከባድ ሥራ በማሠራት አንገላቱን፤ አሠቃዩንም።

7. ከዚያ በኋላ የአባቶቻችን አምላክ (ያህዌ) ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ጩኸታችንን ሰማ፤ ጒስቊልናችንን፣ ድካማችንንና የተፈጸመብንን ግፍ ተመለከተ።

8. ከዚህ የተነሣ እግዚአብሔር (ያህዌ) በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ፣ በታላቅ ድንጋጤ፣ በታምራዊ ምልክትና በድንቅ ከግብፅ አወጣን።

9. ወደዚህ ስፍራ አመጣን፤ ማርና ወተት የምታፈሰውን ይህችን ምድር ሰጠን፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘዳግም 26